Telegram Group & Telegram Channel
#ጾም_በክርስትና_ሕይወት

በዚህ ትምህርታዊ ጹሑፍ ስለ ጾም አራት ነጥቦችን እናያለን
1.የጾም ትርጉም
2.ጾም ያስፈለገበት ምክንያት
3.የጾም ጥቅሞች
4.በምን ዓይነት መንገድ መጾም እንዳለብን፡፡
ከላይ ከ1-4 ተራ ቊጥር የተገለጹትን እንደሚከተለው በዝርዝር እናያለን፡፡

1ኛ/ የጾም ትርጉም
ጾም፡- ማለት ክርስቲያን የሆነ ሰው ሁሉ ለተወሰነ ጊዜና ሰዓት ከእህል ከውኃ ተከልክሎ መቆየት ማለት ሲሆን ከሥጋ፣ ከቅቤና፣ ከእንቁላል ደግሞ እንድንጾምባቸው የተወሰኑ የአጽዋማት ሳምንታት እስኪጠናቀቁ የምንከለከልበት ማለት ነው፡፡ /ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 15/
ከዚህም ጋር ጾም ማለት፡- ዓይን ክፉ ከማየት ጆሮ ክፉ ከመስማት፣ አንደበት ክፉ ከመናገር፣ እጅ ክፉ ከመሥራት በአጠቃላይ ሰውነት የኃጢአት ሥራ ከመሥራት የሚገታበት፣ የሚከለከልበት ማለት ነው፡፡ /ቅዱስ ያሬድ/

ጾም፡- ሁለት ዓይነት ነው ይኸውም
ሀ. የአዋጅ ጾም ነው፡- ይህም በስውር ሳይሆን ሁሉ አውቆት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ የሚጾመው ጾም ነው፡፡ ይህም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት አለው፡፡ “በጽዮን መለከትን ንፉ ጾምንም ቀድሱ ጉባኤውንም አውጁ” /ኢዩ. 2፡15/
ሰባቱ አጽዋማት የአዋጅ ጾሞች ናቸው፡፡ እነዚህም እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡
1. የነቢያት ጾም
2. የገሀድ ጾም
3. የነነዌ ጾም
4. ዐቢይ ጾም
5. የሐዋርያት ጾም
6. ጾመ ድኅነት /ረቡዕና ዓርብ/
7.ጾመ ፍልሰታ
ለ. የግል ጾም ነው፡- የግል ጾም ስንል አንድ ሰው በሠራው ኃጢአት ምክንያት ለንስሓ አባቱ ተናግሮ የሚሰጠው የንስሓ ጾም ሲሆን እንዲሁም አንድ ሰው ስለደረሰበትና በእርሱ ላይ ስለሆነ ነገር ስለሚፈልገው ጉዳይ እግዚአብሔር ተገቢውን መልስ እንዲሰጠው የሚጾመው ጾም ነው፡፡ ለምሳሌ ነቢዩ ዳዊት ልጁ በታመመ ጊዜ ጹሟል፡፡ /2ኛ.ሳሙ. 12፡16/
ነገር ግን በግል ጾም ጊዜ ጾሙ ይፋ ስላልሆነ ራስን መሰወር እንደሚያስፈልግ ታዟል፡፡
ይህንንም አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ሲል ተናግሯል፡፡ “ስትጾሙም እንደ ግብዞች አትጠውልጉ ለሰዎች ሊታዩ እንደ ጾመኛ ፊታቸውን ያጠወልጋሉና አንተ ግን ስትጾም ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ በስውር የሚያይህ አባትህ በግልጥ ይከፍልሃል” /ማቴ. 6፡16-18/ ይህ ቅዱስ ቃል ስለግል ጾም የተነገረ ነው፡፡ በዚህ መሠረት የግል ጾምን ከጿሚው ሰው እና ከእግዚአብሔር ውጭ ማንም ማወቅ የለበትም፡፡

2ኛ/ ጾም ያስፈለገበት ምክንያት
ጾም፡- ያስፈለገበት ምክንያት ልጓመ ሥጋ ስለሆነ ነው፡፡ ሰው ሁልጊዜ የጣመ የላመ ምግብ የማይለየውና እንደልቡ እየበላ እየጠጣ ሳይጾም የሚኖር ከሆነ ለኃጢአት ይጋለጣል፡፡ ይህም በፍትሐ ነገሥት ተጽፏል፡፡ “ከመ ያድክም ኃይለ ፍትወት” (ኃይለ ፍትወትን፣ ሥጋዊ ፍትወትን ያደክም ዘንድ ጾም ታዘዘ) /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15/ እንዲሁም በምንጾምበት ጊዜ ረሀብን፣ ችግርን እናውቃለን፡፡ “ከመ ያእምር ጸዋሚ ሕማመ ረኀብ ወይምሐሮሙ ለርኁባን” (ጿሚ ሰው የረኀብን ችግር ያውቅ ዘንድና ለተራቡ ይራራ ዘንድ ጾም ታዘዘ) /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15/ እንዲሁም “ችግርን የቀመሰ ችግርን ያውቃል” እንዲሉ አባቶቻችን፡፡

3ኛ/ የጾም ጥቅሞች
የጾም ጥቅሞች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡
1.በጾም መንግሥተ ሰማያትን እንወርሳለን፡፡
ይህንንም የሰላም አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ “ስለጽድቅ ብለው የሚራቡና የሚጠሙ ንዑዳን ክቡራን ናቸው እነርሱ ይጠግባሉና” /ማቴ. 5፡6/ ሲል ተናግሯል፡፡
2.በጾም በአገር ላይ የታዘዘው መቅሠፍት ይርቃል፡፡
የነነዌ ሰዎች የዮናስን ትምህርት መሠረት በማድረግ ሦስት ቀን ጾሙ፡፡ ለእነርሱ የታዘዘው እሳት የዛፉን ጫፍ ጫፍ አቃጥሎ ተመልሷል፡፡ /ትን ዮናስ ም. 3 በሙሉ/

3.በጾም ሰይጣን ድል ይሆናል፡፡
“እንዲህ ዓይነት አብሮ አደግ ጋኔን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም” /ማቴ. 17፡21/ ሲል ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌል የተናገረው ቃል ሰይጣን በጾም ድል እንደሚሆን የሚገልጽ ነው፡፡
4.ጾም ከፈተና፣ ከመከራ ያድናል፡፡
ነቢዩ ዳንኤል በጾም ከአፈ አናብስት (ከአንበሶች አፍ) ድኗል፡፡ /ትን. ዳን. ም. 6 በሙሉ/ ሶስና በጾም ከሐሰት ምስክሮች ድናለች፡፡ /መጽ. ሶስና ም. 1 ሙሉ/ ሌሎችም ቅዱሳን በጾም ከፈተና፣ ከመከራ ድነዋል፡፡
5.ጾም ዕድሜን ያረዝማል፡፡
ጾም የመልካም ሥራ ሁሉ መሠረት በመሆኑ ዕድሜን ያረዝማል፡፡
ታላቁ ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በገድላቸው እንደተጻፈው ዕድሜልካቸውን በጾም ነው የኖሩት የእናታቸውን ጡት እንኳን አልጠቡም፡፡ በዚህ ዓለም የኖሩት አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ዓመት ነው፡፡ ሌሎችም ቅዱሳን በጾም የዕድሜ ባለጸጎች ሆነዋል፡፡
6.በጾም ምስጢር ይገለጻል፡፡
አይሁድ አርባ ስድስቱን መጻሕፍተ ብሉያት ቆነጻጽለው ባጠፏቸው ጊዜ ዕዝራ ሱቱኤል አዝኖ አርባ ቀን ጾመ ከዚህ በኋላ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ዑራኤል ሰማያዊ መጠጥ በብርሃን ጽዋ (ጽዋዓ እሳት) ለዕዝራ አጠጣው ዕዝራም ምስጢር ተገልጾለት አርባ ስድስቱን መጻሕፍተ ብሉያት ጽፏል፡፡ /መጽ. ዕዝ. ሱቱ. 13፡36-41/ ሌሎችም ደጋግ ሰዎች በጾም ምስጢር ተገልጾላቸዋል፡፡
7.በጾም ኃጢአት ይሠረያል፡፡
የነነዌ ሰዎች የዮናስን ትምህርት መሠረት በማድረግ ሦስት ቀን ጾመው ኃጢአታቸው ተሠርዮላቸዋል፡፡ /ትን. ዮናስ ም. 3 በሙሉ/ ሌሎችም ሰዎች በጾም ኃጢአታቸው ተሠርዮላቸዋል፡፡ ይህንንም ታላቁ ሊቅ መሠረተ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ያሬድ በዜማ ድርሰቱ እንዲህ ሲል ተናግሯል፡፡ “በጾም ወበጸሎት ይሠረይ ኃጢአት” (በጾምና በጸሎት ኃጢአት ይሠረያል)
8.በጾም ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ይቻላል፡፡
ሊቀ ነቢያት ሙሴ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾሞ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል በቃል ተነጋግሯል፡፡ /ዘዳግም. 9፡9-14/
ነቢዩ ኤልያስም በጾም ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋግሯል፡፡ /1ኛ. መጽ. ነገ. 17፡2/
9.በጾም ልመናችን ይፈጸማል፡፡
እስራኤል በጾም የለመኑትን አግኝተዋል፡፡ /1ኛ ሳሙ. 7፡6-14/ ሌሎችም ቅዱሳን በጾም ልመናቸው ተፈጽሞላቸዋል፡፡
የጾም ጥቅሞች ከላይ ከ1-9 ተራ ቊጥር የተገለጹ ሲሆን ከላይ በርእሱ እንደተገለጸው ጾም የመልካም ሥራ ሁሉ መሠረት ሲሆን በአንጻሩ አለመጾም ደግሞ የኃጢአት ሁሉ መሠረት ነው፡፡ ምክንያቱም ሰው ካልጾመ ለብዙ ኃጢአት ይጋለጣል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ ለሰዎች የተሰጠው የጾም ትእዛዝ ነው፡፡ አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር አዳምና ሔዋንን፡- ይህን ዕፀ በለስ አትብሉ ሲል ከዕፀ በለሱ ተከልከሉ ጹሙ ማለቱ ነው፡፡ እነርሱ ግን አትብሉ የተባሉትን በሉ ከገነት ወጡ ተጎዱ አለመጾም ያስጎዳል፡፡ በዚህ መሠረት ኃጢአት በመብል ምክንያት ወደዓለም ገባ፡፡

4ኛ/ በምን ዓይነት መንገድ መጾም እንዳለብን እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡
ጾም፡- ከትርጉሙ እንደተረዳነው ከእህል ከውኃ ከመከልከሉ ጋር ከክፉ ነገር ከኃጢአት መራቅ ስለሆነ ጾማችን ከክፉ ነገር በመራቅ፣ በቅን ልቡና፣ በንጹሕ ልብ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም ነቢዩ ኢሳይያስ “በምትጾምበት ጊዜ እንጀራህን ለተራበ ብትቆርስ ብርሃንህ እንደንጋት ይበራል የዚያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል ትጮሀለህ እርሱም እነሆ ይልሃል” /ኢሳ. 58፡6-9/ ባለው መሠረት በጾም ጊዜ የጧት ቁርሳችን ለድሆች ከተሰጠ ሰማያዊ ዋጋ እናገኛለን፡፡

tg-me.com/orthodox1/13232
Create:
Last Update:

BY ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴

Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283

Share with your friend now:
tg-me.com/orthodox1/13232

View MORE
Open in Telegram

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴 Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

How Does Bitcoin Work?

Bitcoin is built on a distributed digital record called a blockchain. As the name implies, blockchain is a linked body of data, made up of units called blocks that contain information about each and every transaction, including date and time, total value, buyer and seller, and a unique identifying code for each exchange. Entries are strung together in chronological order, creating a digital chain of blocks. “Once a block is added to the blockchain, it becomes accessible to anyone who wishes to view it, acting as a public ledger of cryptocurrency transactions,” says Stacey Harris, consultant for Pelicoin, a network of cryptocurrency ATMs. Blockchain is decentralized, which means it’s not controlled by any one organization. “It’s like a Google Doc that anyone can work on,” says Buchi Okoro, CEO and co-founder of African cryptocurrency exchange Quidax. “Nobody owns it, but anyone who has a link can contribute to it. And as different people update it, your copy also gets updated.”

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴 from jp

Telegram ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
FROM USA